አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞችን ፅዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ በማድረግ በይበልጥ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ብርሃኑ ዘውዴ ገለጹ፡፡
ከተሞችን የማፅዳት እና አረንጓዴ የማድረግ ክልላዊ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በአርባምንጭ እየተካሄደ ነው።
አቶ ብርሃኑ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ከተሞችን በማዘመን ጽዱ፣ ውብ እንዲሁም መሠረተ-ልማት እንዲሟላላቸው በማስቻል በይበልጥ ለዜጎች ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ጽዳቱ ያልተጠበቀ ከተማ የሕብረተሰቡን ጤና እንደሚጎዳ አስገንዝበው ሁሉም ሰው የከተሞችን ጽዳት በመጠበቅ ረገድ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
ለዚህም ከእያንዳንዱ አባወራ ጀምሮ የሚሳተፍበት የንቅናቄ መድረክ መዘጋጀቱን አስረድተው÷ ንቅናቄው በክልሉ በሁሉም ከተሞች እንደሚተገበር ማሳወቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

