Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ክልል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ።
 
ዛሬ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የችግኝ ተከላ እና ደም ልገሳ በማካሄድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በይፋ ጀምሯል ።
 
የደቡብ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እና የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በአልከሶ ከተማ ወጣቶች ማዕከል ላይ የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት ወጣቶች በህብረተሰቡ እና በአካባቢያቸው የሚታዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እውቀታቸውን ጊዜያቸውን ጉልበታቸው እና በጎ ሀሳባቸውን በማበርከት ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
 
ወጣቶቹ የማህበረሰቡን ጠቃሚ ባህል ወግ እሴት እና ሁለንተናዊ የህይወት መስተጋብሮችን መነሻ በማድረግ በሀላፊነት ስሜት በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡
 
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ ማዳን እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡
 
በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ 250 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል መታቀዱንም የደቡብ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ማስታወቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
በ2012 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ6 አብይ ተግባራት ላይ እንደሚያተኩር የተናገሩት ሀላፊው ተከላ በኮሮና ቫይረስ መከላከል በደም ልገሳ በአካባቢ ጥበቃ በከተምች ጽዳትና ውበት ስራዎች እና በሌሎችም የማህበረሰብ አገልልግሎት ስራዎች ላይ በማተኮር እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡
Exit mobile version