Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስቶ የነበረ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ቀን 9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ፤ እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ነበር ብሏል።

በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጾ፤ በአደጋው መከሰት የአየር መንገዱ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳልነበረ አረጋግጧል።

Exit mobile version