አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪ በዛሬው ዕለት ስራ ጀመረ።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ለኮቪድ19 የናሙና ምርመራ የተዘጋጀው ላቡራቶሪ መርቀው ከፍተዋል።
በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የላቦራቶሪው ስራ መጀመር የምርመራ አቅምን ለማሳደግና ከድሬዳዋና አከባቢዋ ለሚወሰዱ ናሙናዎች በፍጥነት ውጤትን በመግለፅ የመከላከል ሂደቱን እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በሚኒስትር ዴኤታው የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር በኮቪድ 19 ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎችንም ጎብኝቷል።
የቤት ለቤት ልየታ ስራን በጎበኙበት ወቅት በየቤቱ የሚወሰዱ መረጃዎች ለማዕከል በቀጥታ ሪፖርት የሚደረጉ በመሆኑ የተሟላ መረጃ የሚሰጥና የመከላከል ሂደቱን ለማሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

