Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ እንዳሻው ጣሰው ክልላዊ የመኸር የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራ ንቅናቄን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የ2016 ክልላዊ የመኸር የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄን በይፋ አስጀምረዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ንቅናቄውን በክረምት የችግኝ ተከላ በየም ዞን ዴሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ ዲቻ ቀበሌ ማስጀመራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በመርሐ ግብሩ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተጨማሪ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ፣ምክትል ርዕሰ መስተደድር አንተነህ ፈቃዱ፣ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ሶርሞሎና ሌሎችየክልሉና የዞኑ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷ማህበረሰቡ ድህነትን ለማሸነፍ እያከናወነ የሚገኘው የነቃ የልማት ተሳትፎ የሚደነቅ ነው።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ፣ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው÷ በክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ለወጪ ንግድና ኢንዱስትሪ ግብዓትነት የሚውል የግብርና ልማትን በማሳለጥ በርካታ ስኬት ተመዝግቧልም ነው ያሉት።

Exit mobile version