አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ በምርምርና ኢኖቬሽን የተከናወኑ ተግባራትን በስፋት ያስተዋወቀ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
ከግንቦት 11 እስከ 18 ቀን 2016 በሳይንስ ሙዚዬም ሲካሄድ የቆየው ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ የማጠናቀቂያ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኤክስፖው በርካታ ልምዶች የተገኙበት በቴክኖሎጂ የታገዙ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የታዩበትና የተበረታቱበት ነው፡፡
ግል ድርጅቶች ተሳትፎ የታየበት ኤክስፖእንደነበር ጠቅሰው÷ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል።
የስራና ክሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ÷የፈጠራ ሥራዎቹ ከግል ተጠቃሚነት ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራ አመቺ ምህዳር የሚፈጥር ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ ላይ ለዘርፍ አስተዋጽኦ ላደረጉና ተጨባጭ ውጤት ላስገኙ ሽልማትና ዕውቅና ተሰጥቷል።
በታሪኩ ለገሰ