Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አባላት የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም÷ በመንግሥትና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የግብርና እና የመስኖ ልማት ሥራዎቸን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የጋራ ም/ቤት አባላቱ በጎበኟቸው ሥራዎች መደሰታቸውን ገልጸው ፥ ለመሰል የልማት ሥራዎች ከመንግስት ጎን ሆነው እንደሚደግፉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በጉብኝቱ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አክሊሉ አለሙን ጨምሮ የዞኖች የጋራ ምክር ቤቶች የሥራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የሲዳማ ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version