Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ም/ ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ የስራና ክህሎት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።

በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተከናወኑ የልማት ስራዎችና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ተመልክተዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት÷ በኢንስቲትዩቱ ለፈጠራ ሀሳብ ማፍለቂያ እና ለምርምር ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል።

ኢንስቲትዩቱ ከሀገር የልማት ግብ አኳያ ብቁ ሙያተኞችን እያሰለጠነ እንዲሁም በፈጠራና በእውቀት የሚመራ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመፍጠር ላይ ነው ብለዋል።

በየዓመቱ 10ሺህ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ፤ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂስቶች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱንም ጠቅሰዋል።

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሳካ ብቁ የሰው ኃይል ስልጠና እና ምርምር ትኩረት ዋነኛ ትኩረታችን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያን ግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮንስትራክሽንና ሌሎችን ይበልጥ የሚያዘምኑ በርካታ ቴክኖሎጂ በኢንስቲትዩቱ መፈጠራቸውን አንስተዋል።

 

 

Exit mobile version