Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መዲናዋ ከአካባቢ ብክለት ነፃ መሆንን ቀዳሚ ተግባሯ አድርጋ እየሰራች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ ከአካባቢ ብክለት ነፃ መሆንን ቀዳሚ ተግባሯ አድርጋ እየሠራች መሆኗን ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

የዓለም አካባቢ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ51ኛ በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡

አቶ ጃንጥራር በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ አዲስ አበባ ከተማ ከአካባቢ ብክለት ነፃ መሆንን ቀዳሚ ተግባሯ አድርጋ እየሠራች እንደምትገኝ አስታውቀዋል፡፡

አዲስ አበባ ባለፉት ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ በማከናወን፣ የወንዝ ተፋሰሶቿን እየጠበቀች እንዲሁም ኮሪደሮቿንም ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው ብለዋል፡፡

ከከተማችን ፈጣን ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችም ከአካባቢና ማህበረሰብ ጋር ተጣጥመው ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲሄዱ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version