Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሳዑዲ ባለሀብቶች በሆቴል እና ሌሎች የቱሪዝም አገልግሎቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ባለሀብቶች በባለ 5 ኮከብ ሆቴል እና ሌሎች የቱሪዝም አገልግሎቶች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ፡፡

የኢትዮ-ሳዑዲ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለተሳተፉ ባለሀብቶች በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ባለሀብቶቹ በተለይም በባለ 5 ኮከብ ሆቴል ኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍ በሚችሉበት መንገድ ዙሪያ ከቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጋር መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version