Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰኔ 9 ሊሰጥ የነበረው የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን ተዛወረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 9 ሊሰጥ የነበረው የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም መዛወሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በመሆኑ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Exit mobile version