አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 875 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ፥ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 18 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ39 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተጠቁሟል፡፡