አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለተማሪዎች እየተሰጠ ነው፡፡
በዚህም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፣በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ በሐረሪ፣ በሶማሌና በሌሎች ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰጠ ነው፡፡
ተማሪዎችም በፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡