አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ተገንብቶ በቅርቡ ለተመረቀው ሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፀጋዬ አሰፋ እንዳሉት÷ የትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና ስትራቴጂክ ዕቅድ በትምህርት ባለሙያዎችና መምህራን እየተዘጋጀ ነው፡፡
የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተገኝተው ባለሙያዎቹ እያዘጋጁ የሚገኘውን መተዳደሪያ ደንብ፣ ስትራቴጂክ ዕቅድና መዋቅራዊ አደረጃጀት ሂደትን ተመልክተው የሥራ አቅጣጫ መሥጠታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡