አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ ኮሪያ እና ኢትዮጵያ የደን ሀብትን መልሶ ለማልማት እና ቀጣይነት ያለው የደን ልማትን በተለያዩ አካባቢዎች ለማረጋገጥ ሀገራቱ በትብብር ሊሰሩ ነው።
በደን ሀብት ልማት በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነትም የኢትዮጵያ አካባቢ፣ ደን እና የአየር ንብረት ኮሚሽን እና የደቡብ ኮሪያ የደን አገልግሎት ይፋ አድርገዋል።
በዚህ ስነ ስነ ስርዓት ላይም ትብብር ለአረንጓዴ ልማት እና የ2030 ዓለም አቀፍ ግብ የመግባቢያ ስምምነትን ተፈራርመዋል።
ትብብሩ ለአረንጓዴ ልማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ እና የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ቀጣይነት ያለው የደን ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።
ደቡብ ኮሪያ በደን መልሶ ማልማት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ስትሰራ መቆየቷን ገልጻ በዚህ ስራም በአመቱ በትብብር ለአረንጓዴ ልማት ፅህፈት ቤት ተመራጭ መሆኗ ተነግሯል።
ይህ የሰላም ደን ተነሻሽነት የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክት የደን ሀብትን መልሶ በማልማት እና ነፃ ገበያን በመፍጠር አካባቢያዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እና ሰላምን ለማረጋገጥ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ኮሪያ ሄራልድ ዘግቧል።
ደቡብ ኮሪያ የደን ሀብት ሚኒስትር ፓር ቾንግ ሆፍ በኮሪያ ጦርነት የእግረኛ ጦር ለላከችልን ብቸኛዋ አፍሪካዊ ሀገር የሰላም ደን ተነሻሽነት ፕሮጀክት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

