Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሻንጋይ ኤክስፖ የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብርን እውን ለማድረግ ልምድና ተሞክሮ አግኝተናል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ኤክስፖ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ያለውን የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብርን እውን ለማድረግ የሚያግዝ ልምድና ተሞክሮ ማግኘት ችለናል ሲሉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለፁ፡፡

በቻይና – ሻንጋይ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የሻንጋይ 2024 ኤክስፖ ላይ የታደሙት ሚኒስትሯ በማህበራዊ ተስስር ገፃቸው÷ በኤክስፖው በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የመሠረተልማት ዝርጋታና ቅንጅት በከተማና መሠረተ ልማት ሴክተር ትኩረት የሚፈልጉ ስራዎች መሆናቸውን መገንዘብ መቻሉን ጠቅሰዋል።

የስልጡን ከተማ ስርአትና የዘመነ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለዜጎች ማቅረብና በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የመሠረተ ልማት ዝርጋታና ቅንጅት በከተማና መሠረተልማት ሴክቴር ትኩረት የሚፈልግ ስራዎች መሆናቸው በኤክስፖው ማየት ችለናል ነው ያሉት፡፡

በዛው ልክ የከተሞችን ክፍተት በመለየት የበለጠ ለማዘመን መሥራት እንደሚገባ ግንዛቤ መወሰዱን ገልጸዋል።

Exit mobile version