አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይማኖት አባቶችና የከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀው ኮንፈረንስ ”የሐይማኖት ተቋማችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በኮንፈረንሱ ከሁሉም ቤተ ዕምነቶች የተውጣጡ የሐይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ የሐይማኖት አስተማሪዎች፣ የፌዴራልና የክልሎች የሥራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

