Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጀርመን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በጀርመን በመቶዎች የሚቆጠሩ የቄራ ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ።

በሰሜን ምዕራብ ጀርመን  ጉተርሰሎህ  በተባለ የስጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ  ውስጥ የሚሰሩ ከ650 በላይ ሰራተኞች በኮሮኛቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በስጋ ማቀነባበሪያው ከሚሰሩ ሰራተኞች ውስጥ ከ 1ሺህ በላይ ለሚሆኑት ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ÷ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩሰራተኞችም የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል ፡፡

በመሆኑም እነዚህ ሰራተኞችና ከእነርሱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ሁሉ  የምርመራ ውጤታቸው  እስኪታወቅ ድረስ በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ  ተነግሯቸዋል ነው የተባለው።

ይህንንም ተከትሎ ከረቡዕ ከሰዓት  ጀምሮ   በስጋ ማቀነባበሪያው የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ  እንዲቆሙ ተደርጓል።

ከዚያም ባለፈ የአካባቢው ባለስልጣናት እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ በክልሉ  የሚገኙትን ትምህርት ቤቶች እና የህፃናት መንከባከቢያ ማዕከላት ዘግተዋል ፡፡

ቻንስለር አንጌላ ሜርክልም የአካባቢው   ባለስልጣናት የቫይረሱን ስርጭት  ለመቆጣጠር ና ለመከላከል የወሰዱትን እርምጃ  አድንቀዋል።

ጀርመን በትናንትናው ዕለት  በአገሪቱ   የሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶች ላይ እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ እገዳ እንደምትጥል  አስታውቃ ነበር ፡፡

በአውሮፓ  ህብረት ውስጥ ከፍተኛ ህዝብ  የሚኖርባት ጀርመን የአውሮፓ ሀገራትን በከፍተኛ ሁኔታ በጎዳው በዚህ ወረርሽኝ ከ 9 ሺህ በታች ሞት በማስመዝገብና  የበሽታውን ስርጭት በመቆጣጠር ረገድ   የወሰደችው እርምጃ የሚያኮራ መሆኑ ሲነገርላት ቆይቷል።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version