Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መካሄድ ጀመረ፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ስብሰባ በሁለቱ ሀገራት መካከል የልማት ትብብር፣ የጋራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በስበሰባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻውል÷ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና የውጭ ጉዳይ ዳይሬክተር አምባሳደር አንቲፓስ ኒዮክ በበኩላቸው÷ ስብሰባው ሁለቱ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ በጋራ እንዲሰሩ ያግዛል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version