አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡
ከፕሮጀክቶቹ መካከልም በድሬጣያራና ሶፊ ገጠር ወረዳዎች የተገነቡት የድሬጠያራ 2ኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ግንባታ እና የአውበርኸድሌ ታሪካዊ መንደር እድሳት ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም በሐረር ከተማ አባድር ወረዳ ከጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ አምስቱ በሮች አንዱ የሆነው ታሪካዊው የሱቅጣጥ በር እድሳት እና ጥገና ፕሮጀክት ይገኝበታል፡፡
እንዲሁም በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ውስጥ የተገነባው የሐረሪ ክልል የእሳት እና የድንገተኛ አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክት መመቀረቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

