Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የዘንድሮው ክልል አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል።

የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በክልሉ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ እንደሚካሄድም ተመላክቷል።

ከችግኝ ተከላው በተጓዳኝ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና የቀጣይ እቅዶች ዙሪያ የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው እየተመከረባቸው ነው።

ከተረጂነት በመውጣት በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ለማገዘ ክልሉ ያሉትን ጸጋዎችን አሟጦ መጠቀም ትኩረት የተሰጠው ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዛሬ በሚከናወነው መርሃ ግብር በአንድ ጀምበር 10 ሺህ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን የመትከል መርሃ ግብር እንደሚከናወንም ተመላክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአመራር አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

Exit mobile version