Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

እስከ አሁን ከእሪ በከንቱ በፒያሳ አራት ኪሎ ያለውን የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጎብኝዎቹ ባደረጉት ገለጻ በኮሪደር ልማቱ የተቀናጀ የመሰረተ-ልማት መዘርጋቱን ገልጸው÷ ለአብነትም የኤሌክትሪክ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም እና የፍሳሽ ማስወገጃ መሰረተ-ልማቶች ከመሬት በታች መቀበራቸውን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ያለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት እንደሚኖር አመላክተዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከተሞችን ለአገልግሎት ምቹ ከማድረግ ባሻገር ጽዱና ውብ ከተማ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ እና ቤዛዊት ከበደ

Exit mobile version