Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክረምት በጎ ፈቃደኞች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰቡን እያገለገሉ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰማርተው ማሕበረሰቡን እያገለገሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በዚህም ወጣቶቹ በወላይታ ሶዶ፣ ዲላና አርባምንጭ ከተሞች በመሰማራት ማሕበረሰቡን እያገለገሉ መሆኑን የሰላምሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በሶዶ ከተማም ዋዱ ቀበሌ የአቅመ ደካሞችን ቤት በመሥራት የበጎነት ተግባር መፈጸማቸው ተገልጿል፡፡

Exit mobile version