አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ዙሪያ 80 ሚሊየን ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
እነዚህ ሰዎች እስካለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ድረስ በግጭት ፣ አመጽ ፣ ጥቃት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቀያቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ነው ድርጅቱ ያመለከተው፡፡
የዘንድሮውን የዓለም የስደተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ባለፈው አመት ብቻ ወደ 11 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
ይህም ባለፉት አስርት አመታት ከተከሰተው የስደተኞች ቁጥር በሁለት እጥፍ የላቀ ነው ተብሏል፡፡
የሶሪያ ፣ ቬንዝዌላ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ማይናማር ዜጎች ከሁለት ሦስተኛ በላይ የሚሆነውን ስደተኞች ቁጥርን ይይዛሉ ነው የተባለው፡፡
ቱርክ 3 ነጥብ 9 ሚሊየን ሰዎችን ስታስተናግድ በአብዛኛው 10 አመት ካስቆጠረው የሶሪያ ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ናቸው ፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ
Chat Conversation End
Type a message…

