Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 135 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ 135 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የባንኩ ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ13 እድገት ማሳየቱ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህም ከታክስ በፊት 25 ነጥብ 6 ቢሊየን ትርፍ በማግኘት በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 1 ነጥብ 17 ትሪሊየን ብር በላይ ሲሆን፤ የባንኩ ደንበኞች ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊየን በላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ባንኩ ገቢው ሊያድግ የቻለው በዋናነት ለዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ፣ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ምቹ እንዲሆኑ ማስቻሉ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ ማስፋፋት በመቻሉ ነው ተብሏል፡፡

ከሲስተም ማሻሻያ ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለ አግባብ ተወስዶ ከነበረው ብር 801 ነጥብ 4 ሚሊዮን ገንዘብ ውስጥ 99 ነጥብ 34 በመቶ የሚሆነውን  ማስመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ቀሪውን 4 ነጠብ 76 ሚሊዮን ብር ለማስመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ መገለፁን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version