Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ፣የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ፍቃዱ ተሰማ እና ሌሎቸ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የእንስሳት እርባታ እንቅስቃሴን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን መመልከታቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

Exit mobile version