Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የሠላም ጥሪን ተቀብለው የተሐድሶ ስልጠና ያጠናቀቁ ወጣቶች ተመረቁ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ጥሪን ተቀብለው የተሐድሶ ስልጠና ያጠናቀቁ ወጣቶች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ዑመር እና የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አለምነሽ ይባስን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ወጣቶቹ የክልሉ መንግሥት ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ያቀረበውን በውይይት ላይ የተመሠረተ ሠላማዊ ጥሪ ተቀብለው የተመለሱ እና እና የተሐድሶ ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ ናቸው ተብሏል፡፡

Exit mobile version