Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ሚኒስቴሩ በሚያሥገነባቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ከሚሰሩ ስራ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር የሚመሩበት የሶስትዮሽ የጋራ ስምምነት ነው ዛሬ የተፈራረመው፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሃም በላይ (ዶ/ር)÷ ስምምነቱ ፕሮጀክቶቹን በጥራት፣ በፍጥነትና በአጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ ያስችላል ብለዋል፡፡
ከ21 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ ዙር የ12 ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከአምስት ስራ ተቋራጮች እና ከሶስት አማካሪ ድርጅቶች ጋራ የሶስትዮሽ የጋራ ውል ስምምነት መፈረሙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version