Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አስገነዘቡ፡፡

ሚኒስትሯን ጨምሮ የተቋማቸው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እና በመደመር ትውልድ መጽሐፍ የተገነባውን የሐረር ኢኮ ፓርክ ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ሚኒስትሯ በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

የሐረር ኢኮ ፓርክ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት መገንባቱ ለሌሎች ፕሮጀክቶች ተሞክሮ የሚወሰደበት መሆኑን ገልጸው÷ ፓርኩ የክልሉን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በተገቢው ሁኔታ የሚያሳይና ለቀጣይ ትውልድ የሚያስተላልፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጁገል የውስጥ ለውጥ መንገድ ስራም በአካባቢው ያለውን ስነ ምህዳር በጠበቀ መልኩ ማራኪ ሆኖ መሠራቱን ነው የተናገሩት፡፡

Exit mobile version