አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል አስታውቋል።
ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት እንዲያገኙ የፈተና ቁሳቁሶችን አጅቦ የፈተና መስጫ ማዕከላት በማድረስና ለተፈታኝ ተማሪዎች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ማድረጉንም የጋራ ግብር ኃይሉ ገልጿል።
ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡና የተማሪ ቤተሰቦች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም የፀጥታ አካላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት ስለተወጡ የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ምስጋና አቅርቧል።