አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት÷በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ዜጎች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውንም በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡