Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የገዥ ትርክት ግንባታ ሂደትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ገዥ ትርክት ግንባታ ሂደትን ከተግባራዊ ምሳሌዎች ጋር በማስተሳሰር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ብልጽግና ፓርቲ አስገነዘበ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ “የብሔራዊነት ትርክት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ ለ4ኛ ዙር በአዲስ አበባ ከተማ ሲያካሂደው የነበረው ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የሥራ መመሪያ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ÷ የገዥ ትርክት ግንባታ ሂደትን ከተግባራዊ ምሳሌዎች ጋር በማስተሳሰር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የብሔራዊ ገዥ ትርክትን በሕዝብ ዘንድ እንዲናኝ በማድረግ የሚዲያ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

ገዥ ትርክቱ በሐሳብ ገበያው አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ መደበኛ ሚዲያዎችን እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ፕላትፎም የፈጠረው ዕድልና የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመረዳት ለምኅዳሩ የሚመጥን አቅም ማዳበር እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

ስኬቶቻችንን ከእሳቤዎቻችን ጋር በማስተሳሰር በሐሳብ ገበያው በብዙኃኑ ዘንድ ገዢ ሐሳብ እንዲሆን በማስቻል ፖለቲካዊ ጤንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰት መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version