አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው ዘላቂ አካታች ዕድገትን ለማረጋገጥ ለወሰደችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ የዓለም ባንክ ድጋፍ አድረጓል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር አጽድቋል።
ባንኩ እንዳስታወቀው 1 ቢሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ብድር ነው።
የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት የዓለም ባንክ አሁን በቀጥታ ከሚሰጠው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በመጨመር ኢትዮጵያ በጠቅላላው 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ ብቻ እንደምታገኝ ያመለክታል።
ከዚህ በተጨማሪም፦
👉1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)
👉500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
👉320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)
👉1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
👉6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ
👉2 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂ ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል።

