Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር  የሚያዋስናትን ድንበር  ዳግም ልትከፍት ነው

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኬንያ ከጎሮቤቷ ሶማሊያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ከህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እና አሸባሪዎች ጋር በተያያዘ የዘጋችውን ድንበር ዳግም ለመክፈት ማቀዷ ተሰምቷል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ላይ ሀገሪቱ ከሶማሊያ ጋር የምትዋሰንበትን  ድንበር በመዝጋቷ ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይአሉታዊ ተጽእኖ ማድረሱ ተነግሯል ።

አሁን ኬንያ ዘግታ  የቆየችውን ድንበር ዳግም በመክፈት በአካባቢው የሚካሄደው የንግድ እንቅስቃሴ ለመጀመር ማቀዷን  ይፋ አድርጋለች።

ይህንን የመንግስት ውሳኔ ተከትሎ በላሙ አውራጃ  የሚገኙ ከፍተኛ የአሳ አምራቾችና ከሶማሊያ ወደ ኬንያ የሚያስወጡና የሚያስገቡ ነጋዴዎች  የንግድ ልውውጥ በቅርብ ይጀምራሉ ተብሏል።

የሊሙ አውራጃ ኮሚሽነር አይሩጉ ማቻሪያ÷እገዳው የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ  ያስከተለውን ውጤት አስመልክቶ  ዓሳ አጥማጆችና  ነጋዴዎች ቅሬታ ሲያሠሙ መቆየታቸውን ተናግረዋል ፡፡

በአሁኑ ወቅት ዓሣ አጥማጆቹና ነጋዴዎቹ በተለይም በክልሉ ውስጥ ያሉ ነጋዴዎች የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል  እየተሰራ ነው ብለዋል።

አያይዘውም የአካባቢው የኢኮኖሚ ቁልፍ ከሆኑት የዓሳ ምርት ንግድ እና ቱሪዝም  ባለፈ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉን ገልጸዋል ፡፡

የተጎዱትን  የንግድ ዘርፎች ለማደስ ፣ የአካባቢው ደህንነት ኮሚቴ ፣  የመንግስት አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በአካባቢው የሚካሄደውን  የንግድ እንቅስቃሴ  ለመቆጣጠር በመስራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፡- ዴይሊ ኔሽን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version