Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በተለያዩ ርቀቶች የምትሳተፍበት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይደረጋሉ።

በዚሁ መሠረት ቀን 6 ሠዓት ከ5 ላይ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ፣ ኤርሚያስ ግርማ እና አብዲሳ ፈይሳ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ መዲና ኢሳ እና እጅጋየሁ ታዬ ይሳተፋሉ።

በሌላ መርሐ-ግብር ደግሞ ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ፣ ሀብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።

Exit mobile version