Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክዬ አቻቸው ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክዬ አቻቸው ሀካን ፊዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ እና ሀካን ፊዳን ፥ በሶማሊያ እና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባሉ እና በሌሎች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚህም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version