አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ደቡብ ሱዳን የሚጠበቅባትን ዓመታዊ መዋጮ ባለመክፈሏ ከህብረቱ እንዳገዳት ተገለፀ።
ደቡብ ሱዳን 9 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ የአባልነት ዓመታዊ መዋጮን ለአፍሪካ ህብረት ባለመክፈሏ ነው የታገደችው።
ደቡብ ሱዳን ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሚጠበቅባትን ዓመታዊ መዋጮ ባለመክፈሏ መታገዷንም በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ለሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ አረጋግጧል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሀገሪቱ ከአፍሪካ ህብረት መታገዷን በመግለፅ እገዳው ከህብረቱ አባልነት ሳይሆን ስብሰባዎችን ደቡብ ሱዳን እንዳትሳተፍ መሆኑን ገልጿል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል አቀባይ ሃኪም ኤድዋርድ ደቡብ ሱዳን ዓመታዊ መዋጮ ባለመክፈሏ በአፍሪካ ህብረት እገዳ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብለዋል።
ምክትል ቃል አቀባዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከፋይናንስ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ችግሩን እንደሚፈታ ማስታወቃቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

