Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሥተዳደሩ የድሬዳዋ ደወሌ መስመር ሽንሌ መገንጠያ አካባቢ ለትራፊክ ዝግ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካባቢው እየጣለ ከሚገኘው ጠንካራ ዝናብ ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ-ደወሌ የክፍያ መንገድ ከድሬዳዋ ሥድስት ኪሎ ሜትር ርቀት (ቪታ ውኃ ፋብሪካ አካባቢ) የሚገኘው ድልድይ በጎርፍ መሸርሸር ምክንያት ጉዳት ደርሶበት እየተጠገነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጥገናው እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመንገዱ መነሻ እስከ ሽንሌ መገጠያ ድረስ ያለው የመንገድ ክፍል ለትራፊክ ዝግ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከደወሌ ወደ ድሬዳዋ እና በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች የመጀመሪያውን የክፍያ ጣቢያ እንዳለፉ ሽንሌ መገንጠያ ከመድረሳቸው በፊት የድሮው ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስተግራ በኩል የሚገኘውን ተለዋጭ መንገድ እዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

Exit mobile version