Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሁዋዌ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሁዋዌ በኢትዮጵያ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ለማሻሻልና ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ተጠየቀ፡፡

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ከህዋዌ የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ቀጣና ፕሬዚዳንት ጄሪ ቼን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ህዋዌ ያለውን ልምድና አቅም በመጠቀም በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት መረጃ አስተዳደርን ማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት የማዘመን ስራ  እና በኢነርጂ ልማት ዘርፍ እየተደረገ በሚገኘውን የአውቶሜሽን ትግበራ ላይ ከኩባንያው ጋር በትብብር እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።

የኃይል መሰረተ ልማቶችን የማሻሻልና የማዘመን ሂደት ላይም ኩባንያው ተሳትፎ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከማበረታታት አንጻር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ጣቢያችዎችን ለማስፋፋት እንዲሠሩ ጠይቀዋል።

Exit mobile version