Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ አመራሩ ተግዳሮትን በመሻገር ለበለጠ ድል እንዲዘጋጅ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመዘገቡ ምርጥ ውጤቶች ማስፋት እና ተግዳሮቶችን በመሻገር ለበለጠ ድል መዘጋጀት እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስገነዘቡ፡፡

የክልሉ የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ደስታ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አመራሩ እስከ አሁን ለተመዘገበው ምርጥ ውጤት ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ የራሱን ዐሻራ አኑሯል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

እነዚህን ድሎች በማስፋት እና ተግዳሮቶችን በመሻገር አመራሩ ለበለጠ ድል እራሱን እንዲያዘጋጅም አሳስበዋል፡፡

Exit mobile version