አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የጋራ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ መድረኩ እርስ በርስ ለመማማር፣ ተግባራትን በመገምገም ጥንካሬና ክፍተቶችን ለይተን የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የጤና ሥራ የጋራ በመሆኑ ሁሉም በቅንጅት ከሠራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልም በመድረኩ ተገልጿል፡፡