አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ተመራቂዎቹ በምህንድስና፣ በጤና እና በሃብት አሥተዳደር ዘርፍ ትምህርታቸውን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ በዶክትሬት ዲግሪ መከታተላቸው ተገልጿል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ፍጹም አሰፋን (ዶ/ር) ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችና የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።
በሦስት ኮሌጆች እና በአንድ የምርምር እና ልማት ኢንስቲትዩት የተዋቀረው ዩኒቨርሲወቲው÷ በመጪዎቹ ዓመታት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ የመሆን ራዕይ አንግቦ እየሠራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከኢትዮጵያ ተማሪዎች በተጨማሪ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ተማሪዎችንም አሰልጥኖ እያስመረቀ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡