አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር የምክክር ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በይፋ ለኮሚሽኑ አስረከቡ፡፡
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በድሬዳዋ አስተዳደር ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡
ይህን ተከትሎም ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር እና ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ (ዶ/ር) የድሬዳዋ አስተዳደር አጀንዳዎችን በይፋ ተረክበዋል፡፡