አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የኦሮሞ አባገዳዎች ሕብረት ጉባዔ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው ከሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የተወጣጡ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል፡፡
ትውልዱን በማስተማር፣ አንድነትን በማጠናከር እና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ የኦሮሞ አባገዳዎች ሕብረት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የገዳ ሥርዓትን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ መገለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡