Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሲፍ ፋውንዴሽን በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከሕጻናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (ሲፍ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሲፍ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ሐሩራማ በሽታዎችን ጨምሮ በስርዓተ ምግብና መከላከል በሚቻል ምክንያት የሚመጣ ሞትን ለመቅረፍ ባለሙ ፕሮጀክቶች የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ሃላፊዎቹ በውይይታቸው የሲፍ ፋውንዴሽን ፕሮጀክቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሲፍ ትኩረት ለሚሹ በሽታዎች ትኩረት የሰጠ ፕሮጀክት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር መቅደስ ÷ ፋውንዴሽኑ እያሳየ ባለው አፈፃፀም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ትኩረት የሚሹ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ እንደሆነች መጥቀሳቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያላክታል፡፡

ኬት ሃምፕተን በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለፕሮጀክቱ ለሚያደርገው ድጋፍና ተነሳሽነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው÷ በቀጣይ እገዛቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

Exit mobile version