አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ ባለው በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር እስከ አሁን ድረስ 402 ሚሊየን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ እንዳሉት÷ እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር 19 ሚሊየን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በንቃትእየተሳተፉ ነው፡፡
እስከ አሁን ድረስ 402 ሚሊየን ችግኞችን መትከል መቻሉን እና በዚህም 161 ሺህ ሔክታር በችግኝ መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡