አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
በም/ርዕሰመስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስትባባሪ አቶ አሊ መሃመድ እና ሌሎች የክልሉ ግብርና ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች መሳተፋቸውንም የአፋር ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡