Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሁን ካለው እየከፋ እንደሚመጣ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ ሀገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ገና ጣራውን እንዳልነካ እና ከዚህ በባሰ ሀገራቱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ተነገረ ።

የዓለም የጤና ድርጅት ድንገተኛ ህክምና ዳይሬክተር ሚካኤል ሪያን ኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰው ቀውስ በአብዛኞቹ የማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ ሀገራት ስርጭቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

በሀገራቱ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ሊመዘገብ እንደሚችል ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት ፡፡

በበርካታ ሃገራት ባለፈው ሳምንት ከ25 እስከ 50 በመቶ ያክል ወጥ በሆነና እና በአሳሳቢ ፍጥነት በቫይረሱ ሰዎች መያዛቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው በንግግራቸው ወረርሽኙ በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 ሚሊዮን ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በዓለም ዙሪያ በዚህ ወረርሽኝ የመጀመሪያ ወር ከ 10 ሺህ ያነሰ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን ሆኖም ባለፈው ወር ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Exit mobile version