Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ አሥተዳደር የተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከትናንት ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑን የድሬዳዋ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የመማር ማስተማር ሥራው መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመርም ነው የተገለጸው፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት እንደሚደረግም የቢሮው ኃላፊ ሱልጣን አሊይ ገልጸዋል፡፡

በክረምቱ ወቅት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል እና ምቹ አካባቢ የመፍጠር ሥራ ተከናውኗል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚያግዙ የተለያዩ የቴክኖሎጂ እና ሌሎች ግብዓቶች መሰራጨታቸውን ጠቁመው÷ ለመምህራንም የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version