Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ በደረሰ ትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡

በዚህም የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version